26 Aug 2024
የእውቅና ሰርተፍኬት
"ክብረ ለሚገባው ክብር እንሰጣለን !"
--------------
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ሀገር ችግር ውስጥ በገባችበት ወቅት ተቋማቸውን ወክለው ግዳጃቸውን ለተወጡ ሹፌሮች፣ ተቋሙ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ በተሳካ ሁኔታ እንዲፈፀም የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሰራተኞች እና እስከ ጡረታ ጊዜቸው በታማኝነት ሀገራቸውንና ህዝባቸውን ሲያገለግሉ ለነበሩ ስድስት ባለሙያዎች የእውቅና ሰርተፍኬት፣ የሜዳሊያ እና የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ሽልማቱን ያበረከቱላቸው የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አባሶ ናቸው፡፡