የ2016 እቅድ አፈፃጸም እና የ2017 እቅድ ውይይት

26 Aug 2024

የ2016 አፈፃጸም እና የ2017 እቅድ ውይይት

 

አቶ ጀማል አባሶበመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አባሶ ሲሆኑ በንግግራቸውም እንደገለፁት፤ ዲጅታል የአሰራር ስርዓትን በመተግበር በ2016 በጀት አመት ለማከናወን የታቀዱ ተግባራት በተሳካ ሁኔታ መፈፀም መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህንም ውጤት ለማስመዝገብ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተዋል፡፡ ተቋማዊ አሰራር ላይ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ የሚጠበቀውን ውጤት ለማስመዝገብ አስችሏል፡፡ በሀገር ደረጃም ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የቁጥጥር ስራዎች ፣ የ3ኛ ወገን ተሽከርካር ዋስትና አሰራርን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ በለማ የኦንላይ የክፍያ የአሰራር ስርአት መዘርጋት፣ የተሻሻለው የ3ኛ ወገን ደንብ ቁጥር 554/2016 በስራ ላይ መዋሉን እና የትራፊክ ቅጣት ማሻሻያ ደንብ በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚውል አንስተዋል፡፡ በተጨማሪ የትራፊክ አደጋ በ10ሺ ተሸከርካሪ በ2016 በጀት አመት ወደ 20.7 መቀነሱን አንስቷል፡፡ የሞት፣ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መቀነስ ቢቻልም በንብረት ላይ የሚደርስ ጉዳት መጨመሩን አንስተዋል፡፡ አቶ ጀማል አክለውም ተቋማችን በ2020 ዓ.ም በ10 ሺ ተሸከርካሪ የሚደርሰውን ሞት 10 የማድረስ እቅድን ለማሳካት ዘመናዊ የአሰራር ዘዴን በመከተል ጠንካራ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም በለማው የሰው ሃብት ማኔጅመንት ሶፍት ዌር ሰነድ፣ የዜጎች ስምምነት ሰነድ፣ ጥናትና መመሪያዎች እና ደንቦች ቀርበው ሀሳብ አስተያየት ተሰጥቶባቸው የዕለቱ መርሃ ግብር ተጠናቋል፡፡

leaders

 

staff

leader

 

 

 

 

staff
staff