የትራፊክ አደጋ የመረጃ አያያዝ በዲጅታላይዜሽን

28 Apr 2024

የትራፊክ አደጋ የመረጃ አያያዝ በዲጅታላይዜሽን

የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ከፌድራል ፖሊስ ጋራ ለመተግበር የተስማሙበትን የትራፊክ አደጋ የመረጃ ማሰባሰቢያ ስርአትን በዲጅታላይዜሽን ለመተካት በለማው ሶፍትዌር አጠቃቀም ላይ ለሙከራ ትግበራ ከተመረጡ ከተሞች ከአዲስ አባባ፣ ከጅማ፣ ከድሬዳዋ፣ ከባህርዳር ለመጡ የፖሊስ አመራርና አባላት  ለሦስት ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ 

በመርሃ ግብሩም ማጠቃለያ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማ አባሶ፣ ኮሚሽነር ሀብታሙ ካሳ የፌድራል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ሃላፊና የፌድራል ፖሊስ የመንጀል ኢንተለጀንት ዋና መምሪያ ኃላፊ፣ ኮሚሽነር ፋሲል አሻግሬ የፌድራል ፖሊስ የህግና ሰበአዊ መብት መምሪያ ኃላፊ እና የክልል አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ በማጠቃለያውም የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት አስፈፃሚ አቶ ጀማል አባሶ በሀገር ደረጃ የተሻሻለ ዘመናዊ ዲጅታላይዜሽን የአሰራር ስርዓትን ለመዘርጋት የተጀመረችውን ጉዞ በተግባራዊነቱ ላይ በዘርፋችን ትኩርት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም በሀገር አቀፍ ደረጃ የትራፊክ አደጋ መረጃ አያያዝ ስርአት ለማዘመን በለማው ሶፍትዌር ዙሪያ ወደ ተግባር ለመግባት የሙከራ ትግበራውን ለማሰጀመር በተሰጠውን ስልጠና መሰረት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም ቀደም ብሎ ሲሰራባቸው የነበረው የወረቀት አሰራር የትራፊክ አደጋ መረጃ አያያዝ ውስንነት የነበረው እንደሆነ በሀገር ደረጃም ትዝብት ውስጥ የከተተ በመሆኑ የአሰራር ስርዓቱን ለማዘመን የሚያስችል የትራፊክ አደጋ የመረጃ አያያዝ ሲስተም በመጠቀም ትክክለኛውን መረጃ በማደራጀትና በተተንትኖ ለሚመለከተው አካል ለማስተላለፍ እንደሚገባ ኮሚሽነር ሀብታሙ ካሳ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡