04 Apr 2024
የመንገድ ትራፊክ አደጋ መረጃ አያያዝ ሥርዓት
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና የመንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት የመንገድ ትራፊክ አደጋ መረጃ አያያዝ ሥርዓትን(RADMS) በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመተግበር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የብዙ ሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ እና በቢሊየን የሚቆጠር የሀገር ሀብትና ንብረት እያወደመ ያለውን የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የትራፊክ አደጋ መረጃ አያያዝ በቴክኖሎጂ ለማገዝ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ለመፈራረም ነው ብለዋል፡፡ በተጨምርም ክቡር ኮሚሽነር ጀነራሉ የማበለፀገውን ስርዓት በተግባር ለማዋል የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መሆኑን እና በጣም ባጠረ ጊዜ ውስጥ እንደ ሀገር ተተግብሮ በአግባቡ መረጃ ተሰብስበው፣ ተተንትነው መፍትሄዎችን ለማስቀመጥ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ወቅቱን የጠበቀ መረጃ በመለዋወጥ አደጋውን መቀነስ የሚያስችል እርምጃዎችን በመውሰድ እንዲሁም ካስፈለገም የፖሊሲ ለውጥ ለመምጣት፣ መሻሻል የሚገባቸዉን ህጎች ካሉ ለማሻሻል የመግባቢያ ሰነዱ የራሱ ሚና አለው ብለዋል፡፡

ክቡር አቶ ጀማል አባሶ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው የመንገድ ደህንነት እና መድን ፈንድ አገልግሎት ሀገራዊ ትራፊክ አደጋ ጉዳትን ለመታደግ የተቋቋመ ተቋም በመሆኑ ተናግሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በርካታ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ገልፀው በተለይም ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና ከክልል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት የህዝብ ንቅናቄን በመፍጠር በርካታ የሞት፣ የአካል እና የንብረት ውድመትን በመቀነስ ረገድ ውጤታማ ሥራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል። የሀገራችን የመንገድ ትራፊክ አደጋ መረጃ አያያዝ ሥርዓታችንን ለማዘመን እና ታማአንነት ያለው አሠራር ለመዘርጋት የበለፀገውን ሥርዓት ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በጋራ አብሮ ለመተግበር የሚያስችል ስምምነት ላይ በመድረሳችን በጣም ደስ ብሎናል ብለዋል።
በማጠቃልያ መርሃ-ገብሩ ላይ የቀጣይ የሥራ አቅጣጫ መመሪያ በአመራሩ ተሰተዋል።