22 Mar 2024
የዜጎች ስምምነት ሰነድ አዘገጃጀት፣ የቅሬታ አቀራረብ እና አፈታት መመሪያ
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት አመራሮች እና ሰራተኞች ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመጡ ባለሙያዎች የዜጎች ስምምነት ሰነድ አዘገጃጀት፣ የቅሬታ አቀራረብ እና አፈታት መመሪያዎች ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡ የተገልጋዮችን ፍላጎት በሚፈለገው ደረጃ ለመወጣትና የአገልግሎት ተደራሽነት፣ ጥራት፣ ቅሬታና አቤቱታ፣ ፈጠራ እና ቅንጅት እንዲሁም ተመጣጣኝ ክፍያ ስርዓት በመፍጠር ወጥ የሆነ አሰራርን በመከተል የምንሰጣቸውን አገልግሎቶች ማዘመን እንደሚገባ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አዲል አብዱላሂ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል፡፡ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እንደ ሀገር መግባባትን በመፍጠር ዘመኑ የደረሰበትን አሰራር ስርዓት ለመዘርጋት በዜጎች የስምምነት ሰነድ አዘገጃጀት እና የቅሬታ አቀራረብ እና አፈታት መመሪያ ዙሪያ ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመጡ አሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት እንዲሁም ተቋማችን የጥራት ሽልማት ውድድን ለመሳተፍ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ በቀረበ ሰነድ ዙሪያ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በሀገር ደረጃ የሚታየውን የቴክኖሎጂ እና የሀብት አጠቃቀም፣ የዜጎች ተሳትፎ፣ የአቅም እና የችሎታ ውስንነቶችን በመቅረፍ ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ፍትሀዊ የአገልግሎት ስርጭት በመስጠት ነፃና ገለልተኛ አገልግሎት በመስጠት የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡