የተሸከርካሪ አደጋ ተጎጂ ልጆችን ድጋፋ

20 Mar 2024

የተሸከርካሪ አደጋ ተጎጂ ልጆችን ማሳድግ

የፀሃይ ኢንሹራንስ ኩባንያ የተሸከርካሪ አደጋ ተጎጂ ልጆችን ለማሳድግ ተረከበ

 የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ የስራ ክፍል በተሸከርካሪ አደጋ ወላጆቻቸውን ያጡ 5 ህፃናት ለፀሃይ ኢንሹራንስ ኩባንያ ተንከባክቦ እንዲያሳድግ እና እንዲያስተምር አስረክበዋል፡፡ በርክክቡ መርሃ ግብሩም ላይ የአገልግሎቱ የዋና ዳይሬክተር ፅ/ቤት ኃላፊ 

አቶ አዲል አብዱላሂ የእንኳን ደህና መጣችሁና የመክፈቻ ንግግር አድረገዋል፡፡ በንግግራቸውም የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት የተሽክርካሪ አደጋ ተጎጂዎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቀነስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ የአገልግሎቱ የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች የስራ ክፍል ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አያሌው የእለቱን መርሃ ግብር አላማን አስመልክቶ ፁሁፍ አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻም የፀሃይ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና ዳይሬክተር 

አቶ ካሳ ልሳነወርቅ፣ የኩባንያው የማርኬቲንግ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ክቡር የሚያሳድጓቸውን ህፃናት ተረክበዋል፡፡