መንገድ ደህንነትና ድህረ ትራፊክ አደጋ አገልግሎት አሰጣጥ

15 Mar 2024

በመንገድ ደህንነትና ድህረ ትራፊክ አደጋ አገልግሎት አሰጣጥ

በመንገድ ደህንነትና ድህረ ትራፊክ አደጋ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ስልጠና መስጠት ተጀመረ

የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ከክልል እና ከከተማ መስተዳድር ለመጡ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የተዘጋጀውን የመንገድ ደህንነትና የድህረ ትራፊክ አደጋ መድን አገልግሎት አሰጣት ላይ ስልጠና መስጠት ተጀምሯል:: በእለቱ የስልጠና መድክ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁና የመክፈቻ ንግረ ያደረጉት የአገልግሎቱ የድህረ ትራፊክ አደጋ አገልግሎት መድን አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ጫላ ፈይሳ ሲሆኑ በንግግራቸውም እንደገለፁት የመንገድ ደህንነትን በማረጋገጥና የቅድመ ትራፊክ አደጋ መከላከል እና የድህረ ትራፊክ አደጋ መድን አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ስልጠና እንደሚሰጥ ገልፀዋል:: አክለውም የመንገድ ትራፊክ አደጋ የሁሉም አካላት ጉዳይ እንደሆነና ሁሉም የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማድረግ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እንደሆነም አንስተዋል:: በዚህም መሰረት ስልጠናው የመንገድ ደህንነት አለማቀፋዊ ፤ አህጉራዊ፤ ሀገራዊ ገፅታ እንዲሁም ሳይንሳዊ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማረጋገጫ መንገዶች ላይ በአገልግሎቱ የትምህርትና አቅም ግባታ ዴስክ ኃላፊ በሆኑት በአቶ ሳሙኤል ይገዙ ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል:: በመርሃ ግብሩም እንደተገለፀው በ3ኛ ወገን መድን አዋጅ 799/2005 : የተሸከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች የአስቸኳይ ህክምና አገልገሎት አሰጣጥ፣ የካሳ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ እና የቀጣይ የሶስት አመታት እቅድ ላይ ስልጠናና ውይይት እንደሚደረግ ለመረዳት ተችሏል::